Fana: At a Speed of Life!

በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በመንገድ ደህነት ዙሪያ ከተማሪ ወላጆች ጋር የምክክር መድረክ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተካሄደ፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተማሪ ወላጆች ተሳትፈዋል፡፡

በመድረኩ በትራንስፖርት ሚኒስቴር የትራንስፓርት አገልግሎት ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወይዘሮ ፈትያ ደደግባ ÷ በመንገድ ደህንነት አጠቃቀም ዙሪያ ወላጆችን ማስተማር የሚኖረው ሚና ዘርፈ ብዙ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ለተማሪ ወላጆች፣ ለአሽከርካሪ የትዳር አጋሮች እና ለመንገድ ተጠቃሚዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመንገድ አጠቃቀምን ማሳወቅም ማህበረሰቡን ማሳወቅ ነው ያሉት ሃላፊዋ በመንገድ አጠቃቀም እንዲሁም የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

በምክክር መድረኩ የመንገድ ደህንነት 2013 ዓ.ም አፈፃፀም እና በትምህርት ቤት አካባቢ ደህንነቱ የተጠበቀ የመንገድ ደህንነት አጠቃቀም ላይ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት መደረጉን በሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.