Fana: At a Speed of Life!

በወሎ ግንባር ህወሓት ያወደማቸውን መሰረተ ልማቶች በመጠገን የበኩላችን እየተወጣን ነው-የግንባሩ ዕዝ መሃንዲስ መምሪያ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በወሎ ግንባር አሸባሪው ህወሓት ያወደማቸውን የመሰረተ ልማት አውታሮችና ሰራዊቱ ለግዳጅ የሚንቀሳቀስባቸውን የገጠር መንገዶች በመጠገን ለህልውና ዘመቻው የበኩሉን ሃላፊነት እየተወጣ መሆኑን የግንባሩ ዕዝ መሃንዲስ መምሪያ ሃላፊ ተናግረዋል።

መሃንዲስ መምሪያው ሰራዊቱ ለግዳጅ በተሰማራባቸው ቦታዎች ሁሉ ዘልቆ በመግባት ካለው የክረምት ወራት ጋር ተያይዞ በጎርፍ የተበላሹ መንገዶችን እየጠገነ ለተሽከርካሪ ምቹ በማድረግና ጠላት የሚፈጥራቸውን ሰው ሰራሽ መሰናክሎች በማስወገድ እየተመዘገበ ላለው ድል ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ክፍሉ በተቋሙ የቀረበለትን ዘመናዊ የምህንድስና ቁሳቁስ በሙሉ አቅሙ ወደ ተግባር በመቀየር የወገንን የሰው ሃይልና የታጠቃቸውን ከባድ መሳሪያዎች ድልድይ ፈጥሮ በማሻገር የአሸባሪው ቡድን ቅዥት ውጥን እውን አንዳይሆን ማድረጉን ሃላፊው አንስተዋል።

ለስራ በተንቀሳቀሱበት አካባቢ ሁሉ የማህበረሰቡ ድጋፍና እገዛ እንዳልተለያቸው መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.