Fana: At a Speed of Life!

በ2013 በደቡብ ክልል ከ1ሺህ በላይ የትራፊክ አደጋ ደርሷል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በ2013 በጀት ዓመት ከ1ሺህ በላይ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መድረሱን የደቡብ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን “ከጳጉሜ እስከ ጳጉሜ እንደርሳለን!”በሚል መሪ ቃል በወላይታ ሶዶ ከተማ የተለያዩ ፕሮግራሞችን አከናውኗል፡፡

የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ኢንፎርሜሽን ብቃት ዳይሬክተር አቶ መርከበ ታደሰ እንደተናገሩት÷ በ2013 ከደረሰው አደጋ ከ40 በመቶ በላይ የሚሆነው በእግረኞ ላይ የደረሰ ነው፡፡

የአደጋው 35 በመቶ መንስኤም ሞተረኞች መሆናቸውን ነው የተናገሩት ።

በዚህም የ409 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ÷ 23 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል ነው ያሉት።

በትራፊክ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸዉ በሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ የሚገኙ ሰዎችን የመጠየቅ መረሃ ግብር መከናወኑንም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በማቴዎስ ፈለቀ እና በኡስማን መሐሙድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.