Fana: At a Speed of Life!

የድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአንጋፋው ድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ የቀብር ስነ ስርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈፀመ፡፡

የአርቲስቱ የአስክሬን ሽኝት በመስቀል አደባባይ ከተካሄደ በኋላ የቀብር ስነስርዓቱ ቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት ተፈፅሟል፡፡

“ተማር ልጄ” በሚለው ዘመን ተሻጋሪ ዘፈኑ የብዙዎችን ቀልብ የማረከው ድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ነሐሴ 27 ቀን 2013 ባደረበት የልብ ሕመም በ80 ዓመቱ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል፡፡

“ተማር ልጄ ሌት ፀሀይ ነው ላልተማረ ሰው ግን ቀኑ ጨለማ ነው…” እያለ ሚሊየኖችን በዜማው መክሯል።

አንጋፋዉ ሙዚቀኛ አለማየሁ እሸቴ በሚጫወታቸው የሙዚቃ ስራዎቹ ‘ኤልቪስ ፕሪስሊ’ የሚል ቅፅል ስምም ተሰጥቶት ነበር።

ስቀሽ አታስቂኝ” ፣ ” እንደ አሞራ ክንፍ አውጥቼ ልብረራ”፣ ” ማን ይሆን ትልቅ ሰው” ፣ ” ምሽቱ ደመቀ”፣ “አዲስ አበባ ቤቴ” ፣ “የወይን ሃረጊቱ” ፣ “የሰው ቤት የሰው ነው”፣ “ደንየው ደነባ”፤ “ትማርኪያለሽ”፣ “ወልደሽ ተኪ እናቴ” እና ” ተማር ልጄ” ከአለማየሁ እሸቴ ሙዚቃዎች በዋናነት የሚጠቀሱለት ናቸው።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በድምፃዊው ህልፈት የተሰማውን ሀዘን በድጋሚ እየገለፀ ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.