Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለመከላከያ ሰራዊት እና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለመከላከያ ሰራዊቱ እና ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍል 17 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ንጉሴ ምትኩ፥ በጋይንት ግምባር ተገኝተው ለሀገር መከላከያ ሰራዊቱ 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።

ከዚያም ባለፈ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከ6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ በተለያዩ አካባቢዎች ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።

በዛሬው ዕለትም በደቡብ ጎንደር ዞን በህወሓት የሽብር ቡድን ጥቃት እና ውድመት ለደረሰባቸው አካባቢዎች ከ300 ኩንታል በላይ የምግብ እህል ፣ 600 ብርድ ልብስ እና ከተቋሙ ሰራተኞች የተሰበሰበ 12 ኩንታል የተለያዩ አልባሳት ለደቡብ ጎንደር ዞን መስተዳድር አስረክበዋል።

የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አወቀ ዘመነ÷ በነበረው ወረራ በዞኑ በአራት ወረዳዎች ከፍተኛ ውድመት የደረሰ ሲሆን÷ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የዕለት ደራሽ ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ለህብረተሰቡ መረጃን በወቅቱ ከማድረስ ባለፈ ችግሩን ተረድቶ ይህ ድጋፍ ማድረጉ ተቋሙን እና ሰራተኞቹን አመስግነዋል።

በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.