በነገሌና ሻኪሶ 391 ቦንዳ የኮንትሮባንድ ልባሽ ጨርቅና የተለያዩ እቃዎች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በነገሌና ሻኪሶ ከተሞች 391 ቦንዳ የኮንትሮባንድ ልባሽ ጨርቅና የተለያዩ እቃዎች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የጉጂ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ምክትል ዳይሬክተር ዋና ሳጂን ጉተማ ሳፊ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ የኮንትሮባንድ ልባሽ ጨርቅና እቃዎቹ የተያዙት ትናንት ሌሊት ላይ ነው።
ከተያዙት መካከል 391 ቦንዳ ልባሽ ጨርቅ፣ ሶስት ካርቶን ሽቶ፣ አራት ካርቶን ሬዲዮኖች፣ 27 ከለር ቴሌብዥኖች፣ ሁለት ኩንታል ጫማና አራት ኩንታል የሴቶች ሰው ሰራሽ ጸጉር እንደሚገኙበት ተናግረዋል።
የኮንትሮባንድ ልባሽ ጨርቅና እቃዎቹ የሰሌዳ ቁጥራቸው ኮድ 3 – 31227 አአ ኤፍ ኤስ አርና ኮድ 3 -22519 አ.አ አይ ሱዙ በሆኑ የጭነት ተሽከርካሪዎች ሲጓጓዙ መያዛቸውን አመልክተዋል ።
ከህዝብ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ተሽከርካሪዎቹ የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ከሞያሌና ዶሎ አዶ ከተሞች በመጫን ሻኪሶና ነገሌ ከተሞች ለማድረስ በጉዞ ላይ እንዳሉ መያዛቸውን ተናግረዋል።
ፖሊስ የኮንትሮባንድ አዘዋዋሪዎችና አሽከርካሪዎቹ ጨለማን ተገን በማድረግ ለጊዜው በመሰወራቸው አድኖ ለመያዝ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን