Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለ85 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዲሱን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ85 የህግ ታራሚዎች በልዩ ሁኔታ ይቅርታ መደረጉን የክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ገለጸ፡፡
 
በዚህ መሰረትም የልዩ ይቅርታ መመሪያውን መስፈርት ያሟሉ ከመተከል ዞን 31፣ ከካማሽ ዞን 19 እንዲሁም ከአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤት 35 ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓል፡፡
 
የህግ ታራሚዎቹ ይቅርታ የተደረገላቸው የክልሉ ይቅርታ ቦርድ ለይቶ ለክልሉ መንግስት ያቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ተቀባይነት በማግኘቱ ነው ተብሏል፡፡
 
ታራሚዎቹ ከነሐሴ 30ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከማረሚያ ቤት እንዲለቀቁ መወሰኑን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.