Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ለክልሉ ልዩ ኃይል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ለክልሉ ልዩ ኃይል 19 ሚሊየን 292 ሺህ ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ተሰብስቦ በባንክ ገቢ መደረጉን የክልሉ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ገለጸ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር፥ ለመከላከያ ሰራዊት እና ለክልሉ ልዩ ኃይል በክልሉ እስካሁን በአጠቃላይ በገንዘብ 34 ሚሊየን 216 ሺህ በላይ ድጋፍ መሰብሰቡን አስታውቀዋል።
ኮሚቴው የድጋፉን ሂደት አስመልክቶ ባደረገው ውይይትም፣ በክልሉ 1 ሺህ 609 ወጣቶችና የሠራዊት ተመላሾች የመከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል መመዝገባቸው ተገልጿል።
በክልሉ የጸጥታ መዋቅሩን ለማጠናከር በክልሉ 530 የልዩ ኃይል ምልምሎች ወደ ስልጠና እንዲገቡ ተደርጓል ተብሏል።
በአሶሳ ዞንና ከተማ አስተዳደር ብቻ 1 ሚሊየን 95 ሺህ 376 ብር የሚገመት 64 ኩንታል ደረቅ ስንቅ ለመከላከያ ሠራዊት እና ለክልሉ ልዩ ኃይል መዘጋጀቱ ተገልጿል።
በተጨማሪም ለመከላከያ ሠራዊት እና ለክልሉ ጸጥታ ኃይል በዓይነት 47 ፍየል፣ 26 በግ፣ 7 እርድ ከብቶች መሰብሰቡን ከክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.