Fana: At a Speed of Life!

ሀገርን ለማሻገር አንድነት ቀዳሚ ተግባራችን ሊሆን ይገባል  – የድሬዳዋ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሀገርን ለማሻገር በሁሉም መስኮች ተባብሮ አንድነትን ማጠናከርና መረዳዳት ቀዳሚ ተግባር ለሆን እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ፈጡም ሙስጠፋ አሳሰቡ።

በየፌዴራል ጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሰራተኞች አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ80 ችግረኛ ቤተሰቦች የገንዘብና ምግብ ነክ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ከከተማው ዘጠኝ ቀበሌዎች ለተውጣጡ ችግረኞች ድጋፉን ያስረከቡት አፈጉባዔዋና በጉምሩክ ኮሚሽን    የድሬዳዋ

ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ደመላሽ ተሾመ ናቸው፡፡

አፈጉባኤዋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግሮች ለመሻገርና ዜጎችን ለማሻገር አንድነትና ትብብርን ማፅናት ይገባል፡፡

የተቸገሩ ቤተሰቦችን ማሰብና መርዳት መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑንም አመልክተዋል።

የጽህፈት ቤቱ ሠራተኞቹ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ3 ሚሊየን ብር በላይ መለገሳቸውን ተገልጿል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.