Fana: At a Speed of Life!

በንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለ172 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለ172 ሺህ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ገለጹ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማትና ከክልል የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮዎች ጋር በ2013 በጀት አፈጻጸምና በቀጣይ በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት አካሂደዋል።

በኮቪድ-19 ተፈትኖ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፍ ላይ ተፅዕኖ ቢያሳድርም በመቋቋም በኤክስፖርትና በኢንዱስትሪው ዘርፍ ውጤት ተመዝገቧል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ ለ172 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን የጠቀሱት ሚኒስትሩ÷ በችግር ውስጥ በጽናት ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ነው ያሉት።

በኤክስፖርት ዘርፍም 3 ነጥብ 64 ቢሊየን ዶላር ገቢ በማግኘት ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛውን ገቢ ማግኘቷን ጠቅሰው÷ የይርጋለም፣ የቡሬ እና ቡልቡላ አግሮ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉንም ጠቁመዋል።

የኤክስፖርት ምርት በአይነትና በመጠን በመጨመር በበጀት ዓመቱ የእቅዱን 88 በመቶ መሳካት መቻሉ የተገለጸ ሲሆን÷ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ20 በመቶ እድገት አሳይቷል ነው ያሉት።

በቀጣይም ”ኢትዮጵያ ኮቪድ 19 ከሚያደርሰው ተጽዕኖ ጋር ግብግብ እያደረገች ባለችበት ወቅት ስግብግብ ነጋዴዎች ህዝቡን ለማማር የሚያደርሱትን አሻጥር ማስቆም ቀዳሚ ተግባር ነው” ሲሉ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የንግድ አሰራርን መዋቅራዊ በሆነ መንገድ ማሻሻል፣ አምራች ኢንዱስትሪውን የመደገፍ፣ ጠንካራ አሰራር መዘርጋትና የማስፈጸም አቅም ማሻሻል ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠርና ህገ-ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ ስርዓት ለመመለስ ሁሉም የበኩሉን መወጣት ይገባዋልም ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከር ክፍተቶችን በማረም ለመስራት የታቀደው ስራ የተሻለ ውጤት የማስመዝገብ ተስፋው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱል ፈታ ዮሱፍ እና የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ ዳንጌ ቦሩ በበኩላቸው ÷ በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ቢኖርም ቀጣይ የተጠናከረ ስራ መሰራት ይጠበቃል ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.