Fana: At a Speed of Life!

የህወሓት ወራሪ ኃይል የጨፈጨፋቸው ንፁሃን የጅምላ መቃብሮች ተገኙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አረመኔው የህወሓት ወራሪ ኃይል በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ ውስጥ በርካታ ንፁሃንን በግፍ መጨፍጨፉንና የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ገለጸ።
የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የግፍ ጭፍጨፋ የተፈጸመባቸው ከ100 በላይ ንጹሃን ህፃናት፣ እናቶችና አዛውንቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የህወሓት ወራሪ ቡድን ግብዓተ መሬቱን በማፋጠንና ለሕዝባችን ዳግም ስጋት እንዳይሆን በማድረግ ደማቸውን እንደምንመልስ ጥርጥር የለውም ብለዋል።
አቶ ግዛቸው እንዳሉት በጥላቻ የናወዘውና ጭፍጨፋን የዕለት ተዕለት ተግባሩ ካደረገው የህወሓት ወራሪ አድማስ የነካ በደል፣ ሰቆቃና የግፍ ፅዋ ሕዝባችንን ለመታደግ ፍጥነታችንን ጨምረን፥ ማርሻችንን ቀይረን ከያለበት ግብዓተ መሬቱን በመፈፀም ሕዝባችንን ልንታደግ ይገባል።
ሚዲያዎችም ይሄንን እውነት ዓለም እንዲያውቀውና ከወራሪውና ጨፍጫፊው ጋር በምናደርገው ትግል አብረውን እንዲቆሙና ድርጊቱንም እንዲያወግዙት በፍጥነት መዘገብና ቦታው ድረስ በመሄድም ሁኔታውን ማስረዳት እንዳለባቸው ጠይቀዋል።
አቶ ግዛቸው አክለውም በየጫካው እየተፋለሙት ያሉትን ጀግኖች መቋቋም ያልቻለው የህወሓት ወራሪ ኃይል፥ በየቤታቸው የነበሩ አዛውንቶችን፣ ህፃናትንና እናቶችን በያሉበት መንደርና ሰፈር በመግባት ግፍ ፈጽሞባቸዋል። ቤተ ክርስትያን ውስጥ ገብቶ ቀሳውስትን የፍጥኝ በማሰር ጨፍጭፏቸዋል ብለዋል።
የህወሓት ወራሪ ኃይል ቀደም ሲል በሰሜን ወሎ፣ በአፋር ክልል የፈፀመውን አይነት ዘግናኝ ጭፍጨፋ በሰሜን ጎንደር በዳባት ወረዳ በጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ በድጋሜ ፈፅሟል።
ይህ ሰይጣናዊ ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች በአፋጣኝ ግብዓተ መሬቱ እስካልተፈፀመ ድረስ ሌሎች ጭፍጨፋዎችን እንደሚፈፅም ግልፅ ነው ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
39,447
People Reached
2,648
Engagements
Boost Post
1.3K
102 Comments
129 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.