Fana: At a Speed of Life!

የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን የማቋቋም ሃላፊነት አለብን – የጌዴኦ ዞን  አፈ ጉባዔ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጌዴኦ ህዝብ ለመከላከያ ሠራዊት ከሚያደርገው ድጋፍ ጎን ለጎን የወያኔ ወረራ የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን   የመደገፍና የማቋቋም ሃላፊነት አለበት ሲሉ የዞኑ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ጥሪ አቀረበ።

ዋና አፈ ጉባዔዋ ወይዘሮ ምስጋና ዋቄዮ በምክር ቤቱ 19ኛ ማጠቃለያ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ፥ ኮሮናቫይረስ እና አሸባሪው ህውሓት በሀገር ላይ ፈተናዎችን ቢደቅኑም ይህን በመቋቋም ልማትን ለማፋጠን እየተሰራን ነው ብለዋል።

የዞኑ ህዝብ አሸባሪውን ህወሓትና ሸኔን ከማውገዝ ባለፈ ስንቅ በማዘጋጀት፣ ደም በመለገስ እና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ለሠራዊቱ አጋርነቱ ማሳየቱንም ገልጸዋል።

ለሠራዊቱ ድጋፉን ከማጠናከር በተጨማሪ በአሸባሪው ህወሓት ጥቃት በአፋርና አማራ ክልሎች የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲያግዝም ጥሪ አቅርበዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽፈራው ቦጋለ በበኩላቸው ፥ በዞኑ የህልውና ዘመቻውን ከመደገፍ በተጓዳኝ በግብርናው ዘርፍ አበረታች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል።

“በተለይ በቡና ልማት ከ14 ሚሊየን በላይ የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው ችግኞችን በመትከል የቡና ሽፋኑን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት ተሰርቷል”ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.