Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቮሊቦል ብሔራዊ ቡድን የደቡብ ሱዳን አቻውን 3 ለ 2 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ የወንዶች ቮሊቦል ሻምፒዮና ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቮሊቦል ብሔራዊ ቡድን ደቡብ ሱዳን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል ።
ከነሀሴ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሩዋንዳ ኪጋሊ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የአፍሪካ የወንዶች ቮሊቦል ሻምፒዮና እስከ መስከረም 6 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቀጥል መሆኑ ተመላክቷል።
በሻምፒዮናው ኢትዮጵያን ጨምሮ 16 ሀገራት አእየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን፥ውድድሩም በ4 ምድብ ተከፍሎ ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ቮሊቦል ብሔራዊ ቡድን በምድብ 2 ከቱኒዚያ ፣ ናይጀሪያ እና ደቡብ ሱዳን ጋር ተደልድሏል።
በዚህም የኢትዮጵያ ቮሊቦል ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከደቡብ ሱዳን ጋር ባደረገው ጨዋታ 3 ለ 2 ማሸነፉን ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People Reached
395
Engagements
Boost Post
375
6 Comments
14 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.