Fana: At a Speed of Life!

ወጪ ንግድ ከፍተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡ 41 ኩባንያዎች ተሸለሙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ በወጪ ንግድ ከፍተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡ 41 ኩባንያዎች ተሸለሙ።
በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በወጪ ንግድ የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ኩባንያዎች የሽልማትና የዕውቅና መርሃ ግብር ተከናውኗል።
በዚህም ከፍተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡ 41 ኩባንያዎች ተሸልመዋል።
የንግና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልእክት፥ ሕወሃት በፈጠረው ቀውስና ፈተና ውስጥም ሆነን ለብዙ ጊዜ አስቸጋሪ የነበረውን የውጪ ንግድ በተሰራው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ውጤታማ አፈፃፀም ተገኝቷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በበጀት ዓመቱ የአገር ውስጥ ምርቶችን ወደ ውጭበመላክ 4 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ታቀዶ 3 ነጥብ 64 ቢሊየን ዶላር በማግኘይ የእቅዱን 88 በመቶ አሳክቷል።
በ2014 በጀት ዓመት አሰራርን በማጠናከር አዳዲስ ምርቶችንና መዳረሻዎችን መጨመር፣ የአሰራር ማነቆዎችን መፍታትና አሰራር ማዘመን ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል ሚኒስትሩ።
የዕውቅና መርሐ ግብሩ ዓላማም ተወዳዳሪ ላኪዎችን ለመፍጠርና ለማበረታታት መሆኑን ተናገረዋል።
ባለሃብቶችና ላኪ ደርጅቶች አገር አሁን ያለችበትን ሁኔታ በመገንዘብ ኢኮኖሚያዊ አሻጥርን እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People Reached
5
Engagements
Boost Post
5
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.