Fana: At a Speed of Life!

የአሸባሪውን መቃብር በማፋጠን ላይ እንገኛለን – የሶማሌ ልዩ ኀይል አባላት

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሕዝብ እና መንግሥት የሰጠንን አደራ ተረክበን የአሸባሪውን መቃብር በማፋጠን ላይ እንገኛለን” በወሎ ግንባር የተሰለፉ የሶማሌ ልዩ ኀይል አባላት።

ሀገርን ለማፈራረስ እቅድ ነድፎ ወረራ የፈጸመው አሸባሪው የትህነግ ቡድን በኢትዮጵያዊያን በጋራ ትግል በመደምሰስ ላይ ይገኛል።

ኢትዮጵያዊያን በአንድነት በተሰለፉበት አውደውጊያ የሶማሌ ልዩ ኀይልም የሕዝብና የመንግሥትን አደራ ተቀብሎ ጠላትን መፋለም ከጀመረ ወራቶች ተቆጥረዋል።

አሸባሪው የትህነግ ቡድን በኢትዮጵያ ላይ ያሴረውን እኩይ ዓላማ ለመበጣጠስም የልዩ ኀይል አባላቱ ዛሬም በወሎ ግንባር ጠላትን እየደመሰሱ ናቸው።

ሻለቃ ሪያድ ጎሌድ ከልዩ ኀይል አባላቱ አንዱ ሲሆኑ÷ ከሕዝቡ የተሰጠን አደራ ከባድ ስለሆነ አደራችንን ተቀብለን ለሰንደቅ ዓላማችን እስከመጨረሻው እንዋደቃለን ብለዋል።

ኢትዮጵያ በቃላት ለመግለጽ የሚያስቸግር ሚስጥር ያላት ሀገር ናት የሚሉት ሻለቃ ሪያድ÷ እኔ ስሞትላት ኢትዮጵያ አንድነቷን አጠናክራ ደምቃና ፈክታ ለዓለም ትታያለች ብለዋል።

ሂሳብ አወራርዳለው ብሎ በቅዥት የናወዘው ቡድን አሁን ልኩን እያገኘ ነው፤ ለዚህም ተራሮቹ ሁሉ ምስክሮች ናቸው ሲሉ መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ሌላኛው የሶማሌ ልዩ ኀይል አባል የሱፍ አህመድ ኢትዮጵያዊነት ደሜ ነው፤ በርካታ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠን የመጣነው ለኢትዮጵያችን ዘብ ለመቆም ነው ብሏል።

በገቡባቸው አውደ ውጊያዎች ሁሉ የሽብር ቡድኑን አባላት በመደምሰስ ላይ መሆናቸውንም ተናግሯል።

አሸባሪው የትህነግ ቡድን በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የሚያናፍሰው ፕሮፖጋንዳ ፍጹም ከእውነታው የራቀ እንደሆነ የሚናገረው የሱፍ አህመድ ኢትዮጵያውያን ተባብረው ወደ መቃብር እያወረዱት እንደሆነ ተናግሯል።

በድላችን ገስግሰን የኢትዮጵያ አንድ አካል የሆነችውን ትግራይንም ነጻ እናወጣለን ያሉት የልዩ ኀይል አባላቱ÷ እስካሁን በነበረው ጉዞ የማኅበረሰቡ ድጋፍ በጣም ከፍተኛ እንደነበርም ጠቅሰዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.