Fana: At a Speed of Life!

የዳያስፖራውን ጉብኝት የሚያስተባብር ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 03፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያ የሚያካሂዱት ጉብኝት የሚያስተባብር የልዑካን ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ገባ።
 
የልዑካን ቡድኑ ቦሌ አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የቱሪዝም ኢትዮጵያ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።
 
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ተግባር ምክር ቤት ባዘጋጀው “እንቁጣጣሽ ኢትዮጵያ የፍቅር ጉዞ” በሚል መሪ ሀሳብ መርሃ ግብር ከጳጉሜን ወር 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም የሚካሄድ ነው።
 
ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት መርሃ ግብሩን የሚያስተባብሩት ስድስት የምክር ቤቱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ናቸው።
 
በመርሃ ግብሩ ከሰሜን አሜሪካ፣ እስያ፣ አፍሪካ፣ አውሮፓና መካከለኛው ምስራቅ የሚመጡ 500 ዳያስፖራዎች የሚሳተፉበት ነው።
 
በመርሃ ግብሩ ዳያስፖራው “አባይን እንጎብኘው” በሚል መሪ ሀሳብ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ እንደሚጎበኝና የግድቡን ሰራተኞች እንደሚያበረታቱም ይጠበቃል።
 
የሸገር ማስዋብና በገበታ ለአገር ፕሮጀክት የተካተተው ጎርጎራ የጉብኝአካል ይሆናል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
 
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.