Fana: At a Speed of Life!

በእድሳት ላይ የነበሩ 1ሺህ 845 ቤቶች ለባለቤቶቹ እርክክብ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመልካምነት ቀን የቤት እድሳት ሲደረግላቸው የነበሩ ወገኖችን ቤት በማስረከብ እየተካሄደ ነው፡፡
በዚህም በሁሉም የመዲናዋ ወረዳዎች 1ሺህ 845 የአረጋዉያን፣ የአካል ጉዳተኞችና የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት የማደስ ተግባር ተጠናቆ እርክክብ ተደርጓል፡፡
ቤት የማደስና መሰረታዊ የቤት ቁሳቁስን የማሟላት በጎ ተግባር በአረጋዉያኑ፣ በአጠቃላይ እገዛ በተደረገላቸዉ ወገኖች ላይ የሚፈጥረው “የወገን አለኝ” ስሜት ጥልቅ ነው ሲሉ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል፡፡
ወይዘሮ አዳነች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ ለሰሩ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.