Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ አማራ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈናቃዮችና ጸጥታ ሃይሎች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ አማራ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለተፈናቃዮች እና ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ለበዓል መዋያ የሚሆኑ የተለያዩ ድጋፎችን አደረጉ፡፡

የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ፣ የመቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲና የወሎ ዩኒቨርሲቲ በጋራ በመሆን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በደሴ ከተማ በተለያዩ መጠለያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና በወሎ ግንባር በውጫሌ አካባቢ አሸባሪው ህወሓትን ለመደምሰስ እየተፋለሙ ላሉ የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ አባላት ነው ድጋፍ ያደረጉት፡፡

ዶክተር ንጉስ ታደሰ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዲንት እንደተናገሩት÷ እንደ ሀገር የገጠመንን የህልውና አደጋ በጋራ ለመመከትና ለማረጋገጥ በማሰብ በምስራቅ አማራ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት ፈጥረው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡

በዚህም ብርድ ልብሶች፣ ዘይት፣ የስንዴና የጤፍ ዱቄት እንዲሁም ሰንጋዎችን በአጠቃላይ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ገንዘብ ወጪ በማድረግ ድጋፉ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

የወሎ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ወቅት እንደዚህ አይነቱ ድጋፍ ቤት ንብረታቸውን ጥለው የመጡ ወገኖች በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ የሚያደርግ እና በግንባር እየተፋለሙ ላሉ የሀገር መከላከያ አባላት እንዲሁም የአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻዎችም ደጀንነትን ማስመስከር መሆኑን አስታውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አማረ ምትኩ በበኩላቸው÷ ሃገር በችግር ላይ ባለችበት ወቅት ቀዳሚው መፍትሄ የሚሆነው አንድነትን ማጠናከር መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ይህንንም ለማረጋገጥ በዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ በቅንጅት ለመስራት ወሎ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በይከበር አለሙ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.