Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ ተግባራት ላይ በተሰማሩ ከ80 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉና በህገወጥ ተግባር ውስጥ ሲሳተፉ በተገኙ ከ80 ሺህ 641 በላይ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በህግ ማስከበር ዘመቻው እየተገኘ ያለውን ድል ለመቀልበስ በህገወጥ ተግባራት ውስጥ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙ የንግድ ተቋማትን በመለየት እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ሚኒስቴሩ ዶላርና ምርት የደበቁ፣ ያልተገባና ምክንያታዊ የሆነ የዋጋ ጭማሬ በማድረግ ለአሸባሪ ቡድኑ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

በዚህ መሰረትም 80 ሺህ 641 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን÷ከነዚህ ውስጥ 520 የንግድ ድርጅቶች ላይ የንግድ ፈቃዳቸው ተሰርዟል፡፡

ከዚህ ባለፈም 257 የንግድ ድርጅቶች ላይ የእገዳ እርምጃ ሲወሰድ÷ በ2 ሺህ 230 የንግድ ተቋማት ላይ ደግሞ ክስ መመስረቱን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

ያለምንም ኢኮኖሚያዊ ምክንያትና የአቅርቦት ችግር ያልተገባ ዋጋ በመጨመር ህገ ወጥ የሆነ ገንዘብ ለማጋበስ የሚሰሩ መኖራቸውን የጠቆሞው ሚኒስቴሩ÷ በተለይ የህግ ማስከበር ዘመቻ እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት በእንደዚህ ዓይነት ተግባር ላይ የሚሳተፉትን አካላት መንግሥት እንደማይታገስ ተመላክቷል፡፡

ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከመረጃና ደህንነት፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን እንዲሁም ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የተውጣጣ በሚኒስትሩ የሚመራ ግብረ ኃይል ተዋቅሮ በጉዳዩ ዙሪያ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይም የተጠናከረ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.