Fana: At a Speed of Life!

በበጀት ዓመቱ ከወርቅ ወጪ ንግድ 671 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 በጀት ዓመት ከወርቅ ማዕድን የወጪ ንግድ ከ671 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን ከማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በበጀት ዓመቱ ከወርቅ ማዕድን 637 ሚሊየን ዶላር ማግኘት ታቅዶ በአጠቃላይ 9 ሺህ 384 ነጥብ 284 ኪሎ ግራም ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቦ ከዕቅድ በላይ ገቢ ለማግኘት ተችሏል።
ከወርቅ በተጨማሪ ከሌሎች ማዕድናት 10 ነጥብ 42 ገቢ ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።
በበጀት ዓመቱ በአምራች ደረጃ በኩባንያዎች የተመረው የወርቅ መጠን 788 ነጥብ 25 ኪሎ ግራም ሲሆን፥ በባህላዊ አምራቾች ድግሞ 8 ሺህ 596 ኪሎ ግራም ወርቅ ተመርቷል።
የኢትዮጵያ የኤክስፖርት ማዕድናት የሚባሉት ወርቅ፣ ታንታለም፣ የጌጣጌጥ ማዕድናት እና እብነበረድ ናቸው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.