Fana: At a Speed of Life!

መልካምነት የ1 ቀን ብቻ ሳይሆን የ365 ቀናት ተግባር ነው-ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ተገኝተው ለአቅመ ደካሞች እና አረጋውያን ማዕድ አጋርተዋል፡፡
ወረዳው በርካታ ችግሮች ያሉበት ስለመሆኑ ግንዛቤው አለኝ ያሉት ፕሬዝዳንቷ የዜጎችን ኑሮ በዘላቂነት ለማሻሻል ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡
በተለይ ሴቶች በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው ኑሯቸውን በዘላቂነት እንዲያሻሽሉ የሚያስችላቸውን መንገድ ለመፍጠር ስራዎች መጀመራቸው ገልጸዋል፡፡
በአካባቢው ወጣቶች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉበት ቦታ ለማመቻቸትም ጥረት እየተደረገ ነው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
መጪው ቀን የበዓል በመሆኑ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ ያደረጉት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ÷በመልካምነት የሚሰሩ ስራዎች በዘላቂነት የዜጎችን ህይወት የሚያሻሽሉ እና መሬት ወርደው የሚታዩ ሊሆኑ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.