Fana: At a Speed of Life!

የመልካምነት ቀንን አስመልክቶ ከ1 ሺህ በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመልካምነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በወዳጅነት አደባባይ የማዕድ ማጋራት እና የተለያዩ ድጋፎች አድርጓል፡፡
 
በዚህምለ1ሺህ አቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራት የተቻለ ሲሆን÷ ለ272 አካል ጉዳተኞች ደግሞ የዊልቸር እና ሌሎች ድጋፎች ተበርክቷል፡፡
 
ጳጉሜ 3 የመልካምነት ቀን ብሎ የሰየመው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መልካምነት ከስያሜ ባለፈ መኖርንም ስለሚጠይቅ ለዚሁ ምሳሌ ይሆን ዘንድ በዛሬው ዕለት ድጋፍ ተደርጓል ነው የተባለው፡፡
 
በመርሃ ግብሩ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ መልካም ነት ፀጋ ነው፣ ይህን ፀጋ አውጥተን በሌሎችም ላይ መዝራት ይገባል ብለዋል፡፡
 
ኢትዮጵያዊ እሴትን በመተግበር በ2014 በመልካምነት ማሳለፍ ይገባል ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
 
መልካምነት መገለጫዎቹ ብዙ ናቸው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ÷ነገር ግን ከሁሉም በላይ በቀን አንድ ጊዜ መብላት ለሚከብዳቸው ወገኖች ማዕድ ማጋራት በልዩነት ይቀመጣል ነው ያሉት፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.