Fana: At a Speed of Life!

“መቶ ለወገኔ” የተሰኘው የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በጋምቤላ ክልል በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና በህወሓት የሽብር ቡድን ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል “መቶ ለወገኔ” የተሰኘ ንቅናቄ በጋምቤላ ክልል በይፋ ተጀምሯል፡፡

የጋምቤላ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሯች ጎች “መቶ ለወገኔ” የድጋፍ ንቅናቄ በተለይ ወጣቶች የሚሳተፉበት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ገቢው በግንባር ላይ ሀገራቸውን ከአሸባሪው ህወሓት በመከላከል ላይ ላሉ ጀግኖችና አሸባሪው ቡድን በተለያዩ አካባቢዎች ባደረሰው ጥቃት ለተፈናቀሉ ወገኖች እንደሚውል ተናግረዋል፡፡

በንቅናቄው እንደ ሀገር ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ የሚጠበቅ ሲሆን ÷180 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ጠቅሰው እንደ ክልልም 5 ሚሊየን ብር ለማሰባሰብ እየተሰራ መሆኑን መግለፃቸውን ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.