Fana: At a Speed of Life!

ባለሃብቶችና ላኪ ድርጅቶች የኢኮኖሚ አሻጥርን እንዲከላከሉ ተጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ባለሃብቶችና ላኪ ድርጅቶች ወቅታዊውን ሃገራዊ ሁኔታ በመገንዘብ ኢኮኖሚያዊ አሻጥርን እንዲከላከሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል በ2013 በጀት ዓመት በወጪ ንግድ ዘርፍ የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ኩባንያዎች ትናንት ማምሻውን ዕውቅናና ሽልማት ሰጥተዋል።

በዚህ ወቅትም ባለሃብቶችና ላኪ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ላይ ውስጣዊና ውጫዊ ጦርነት በተቃጣባት በአሁኑ ወቅት ኢኮኖሚያዊ አሻጥርን እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርበዋል።

እናቶች ልጆቻቸውን ለሃገር ህልውና በሚልኩበት ወቅት በየቦታው በኢኮኖሚ አሻጥር ሕዝብን የሚጎዱ አካላትን በጋራ ልንታገል ይገባል ነው ያሉት ሚኒስትሩ።

ባለሀብቶች የሚያመርቷቸውን ወጪ ምርቶች መጠንና ጥራት በዓለም ገበያ እንዲወዳደሩ፣ የስራ ዕድል እንዲፈጥሩና ሃገራዊ ምርት እንዲያሳድጉ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.