Fana: At a Speed of Life!

ለአዲስ አመት የስጋ ውጤቶችን በጥራትና በተመጣጠነ ዋጋ ለማድረስ ዝግጅት ተደርጓል-ቄራዎች ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአዲስ አመት የስጋ ውጤቶችን በጥራትና በተመጣጠነ ዋጋ ለማድረስ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ገለጸ።

የድርጅቱ የኢንፎርሜሽንና ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል፤ ድርጅቱ ለ2014 አዲስ ዓመት ከ2 ሺህ 500 በላይ የዳልጋ ከብት እና ከ1 ሺህ 500 በላይ በግና ፍየሎችን ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ለህብረተሰቡ ስጋውን ተደራሽ ለማድረግ 40 ዘመናዊ የቄራ ተሽከርካሪዎች መዘጋጀታቸውን ጠቁመው ÷ለበዓሉ ህብረተሰቡ ከንጋቱ 11 ሰአት ጀምሮ ወደ ድርጅቱ በሬ ወይም በግና ፍየል በማምጣት ከ30 እስከ 40 ደቂቃ ባለ ጊዜ አሳርዶ መውሰድ ይችላል ብለዋል።

በዋናው መስሪያ ቤት እና አቃቂ በሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮ በሚገኙ ሱቆች በኪሎ የበግ ስጋ 210 ብር እንዲሁም የበሬ ስጋ በ285 ብር መግዛት እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

ከዚህ ውጭ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እና ንፅህናው ያልተጠበቀ ስጋ በመጠቀም ማህበረሰቡ ኮሮናን ጨምሮ ለተለያዩ በሽታዎች እንዳይጋለጥ አቶ አታክልቲ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.