ኢትዮጵያ እና ጋና በሁለትዮሽና በአፍሪከ ጉዳዮች ላይ በጋራ ይሰራሉ-ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጋና ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ÷እኔን እና የልዑካን ቡድኔን በአክራ በሚገኘው ቤተ መንግሥታቸው ተቀብለው በበርካታ ጉዳዮች ላይ ስላደረግነው ውይይት ለፕሬዚዳንት ናና አኩፎ-አዶ አድናቆቴ ይድረሳቸው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ጋና በሁለትዮሽ እና የጋራ ትኩረት በሆኑ የአፍሪካ ጉዳዮች ላይ በቅርበት ይሠራሉም ነው ያሉት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!