Fana: At a Speed of Life!

አረንቻታ ሚዲያ ኮምቦልቻ ለሚገኙ መከላከያ ሰራዊት አባላት ቤተሰቦች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አረንቻታ ሚዲያ ኮምቦልቻ ለሚገኙ መከላከያ ስራዊት አባላት ቤተሰቦች ለበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ፡፡

ሚዲያው ለበዓል መዋያ ያሰባሰበውን ድጋፍ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ ፣የአማራ ክልል ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ፣ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ ፍቅረማርያም ደጀኔ፣ የኮምቦልቻ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር አህመድ የሱፍ፣ ሸህ ሁሴን መሐዲ እና ቆሞስ አባ ተስፋሚካኤለ ደሳለኝ ለመከላከያ ሰራዊት አባላት ቤተሰቦች አስረክበዋል፡፡

በዕለቱ ሸህ እንድሪስ መሐመድ 100 ሺህ ብር ለአጣዬና አካባቢው ተፈናቃዮች ማቋቋሚያ መለገሳቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

ሀገራችን የምትቀየረው እንደዚህ አይነት ቅንና መልካም ሰዎች ሲበዙ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሁላችንም ለመስጠት እጃችን የሚዘረጋ ይሁን ሲሉ አሳስበዋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.