Fana: At a Speed of Life!

ከሲሚንቶ ፋብሪካዎች በስተቀር ሌሎች በዋዜማው ከዋናው የኃይል ቋት ኤሌክትሪክ እንዳይጠቀሙ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሲሚንቶ ፋብሪካዎችና ከኤክስፖርት ኢንዱስትሪዎች በስተቀር ሌሎች ኢንዱስትሪዎች በበዓሉ ዋዜማ ከዋናው የኃይል ቋት ኤሌክትሪክ እንዳይጠቀሙ ተጠየቀ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበዓሉ በዋዜማና በበዓሉ ዕለት የኤሌክትሪክ ኃይል ሊያጋጥም የሚችለውን የኃይል መቆራረጥ መቀነስ እንዲያስችል እንዲሁም ከተከሰተም በአፋጣኝ የጥገና ስራ ለማከናወን ቡድን አዋቅሮ የቅድመ ዝግጅት ስራውን ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

ሆኖም ከወቅቱ ክረምት ወቅት ጋር ተዳምሮ ሊከሰት የሚችለውን የኃይል መዋዠቅንና መቆራረጥ ለመቀነስ ከሲሚንቶ ፋብሪካዎችና በኤክስፖርት ዘርፍ ከተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ውጪ ያሉ ሌሎች ኢንዱስትሪዎች በአዲስ ዓመት ዋዜማ ማለትም ጳጉሜ 5 ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ድረስ ከዋናው የኃይል ቋት ኤሌክትሪክ ሙሉ ለሙሉ ባለመጠቀም ሊፈጠር የሚችለውን ጫና እንዲቀንሱ ተጠይቋል፡፡

ደንበኞችም በቤት ውስጥ የሚገለገሉባቸውን የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች ኃይል ቆጣቢና ለአደጋ የማያጋልጡ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ተቋሙ አሳስቧል፡፡

በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ኃይል ጭነት በማይበዛበት ሰዓታት በተለይ ከምሽቱ 4 ሰዓት ሰዓት እስከ ንጋቱ 11 ሰዓት ባሉት ጊዜያት ቢጠቀሙ የተሻለ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማግኘት ባለፈ የኤሌክትሪክ መቆራረጥንም ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ማስታወቁን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.