Fana: At a Speed of Life!

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ሰራዊቱን በማበረታታት ረገድ ያደረጉት ድጋፍ ከፍተኛ ነው- አቶ ርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ በሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ማዕከል የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አበረታትተው ለተመለሱ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች አቀባበል አደረጉ፡፡

ርሰ መስተዳድሩ ከክልሉ ለተውጣጡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በተዘጋጀ የአቀባበል መርሃ ግብር ላይ እንደገለጹት÷ በሀገራችን እና በህዝባችን ላይ ያንዣበበውን ጦርነት ለመመከት የክልሉ ህዝብ ያደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ነው።

ጠላቶቻችን በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ሊሰነዝሩ ቀርቶ ዳግመኛ እንዳያስቡ የሚያደርግ ትምህርት እስኪያገኙ ድረስ በሁሉም መስክ የጀመርነው ዘመቻ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡

የክልሉ ህዝብ ለህልውና ዘመቻው የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን የጠቆሙት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ልጆቹን መርቆ ወደ ግንባር በመሸኘት አኩሪ ታሪክ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችም በሙያቸው ሰራዊቱን በማበረታታት ረገድ ያደረጉት ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበር ነው የተናገሩት፡፡

የሀገሬ ጉዳይ ይመለከተኛል በሚል እሳቤ ለሰራዊቱ እየቀረበ ያለው የኪነ ጥበብ ስራ ሀገራዊ ስሜትን ከፍ የሚያደርግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እንደገለጹት÷ የመከላከያ ሰራዊት ለሀገር ክብር እየከፈለ ያለውን ዋጋ በአካል በመገኘት መመልከት በመቻላቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።

ለሰራዊቱ ከገንዘብ መዋጮ ባለፈ በልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ስራዎች በመደገፍ ለህልውና ዘመቻው የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡም ነው የገለፁት፡፡

የክልሉ መንግስት ሙያዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.