Fana: At a Speed of Life!

ወራሪውና አረመኔው ትህነግ የህፃናትን ህይወት ቀጥፏል፤ ቤተሰብን አፍርሷል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጧሪዎቻችንንና የዓይናችን ማረፊያ የሆኑ ልጆቻችንን በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ተነጥቀን፤ በሰው ቤት ተጠግተን ለመኖር ተገደናል ሲሉ ጉዳት የደረሰባቸው የጭና ቀበሌ አረጋውያን ተናገሩ።

አረጋውያኑ ወላጆች እንደመሰከሩት “ወራሪውና አረመኔው ትህነግ የህፃናት ልጆችን ህይወት ቀጥፏል፤ ቤተሰብን አፍርሷል’’።

አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ቀበሌ በፈፀመው ጅምላ ጭፍጨፋ ጧሪ ልጃቸውንና የልጅ ልጃቸውን ያጡት አረጋውያን ወላጆች ወራሪው ቡድን ሀብት ንብረታቸውን ሲዘርፍና ሲያወድም ቆይቷል።

በተለይም ልጆቻቸው በመግደሉ ሀዘናቸው መራር እንደሆነባቸው በስፍራው ለተገኙት የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋዜጠኞች ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በዘመድ ቤት ተጠግተው እንደሚገኙ የተናገሩት አቶ ባዜ ዘውዱና ወ/ሮ ገዳምነሽ መለሰ÷ ቀሪ ዕድሜያችንን በሀዘንም ቢሆን ያለተጨማሪ ችግር እንድንቆይ መንግስትና ህዝብ አስፈላጊውን ድጋፍ ያድርግልን ሲሉ ጠይቀዋል።

ሟች ቄስ ጥፍጥ በዜ የቤተክርስቲያን ገበዝና በእርሻ ስራ ወላጅና ቤተሰቦቻቸውን ያስተዳድሩ የነበሩ ሲሆን÷ ከወንድ ልጃቸው ጋር በግፍ እንደተገደሉባቸው የሟች ሚስት ወ/ሮ ደስታ ሰጠኝ ተናግረዋል።

አረጋውያንን፣ ሴቶችና ህፃናትን ያለ ረዳት ያስቀረውን የትህነግ ወራሪ ቡድን ሁሉም ሊዋጋውና ከምድረ ገፅ አጥፍቶ ፍትህን ሊያሰጠን ይገባል ያሉት የሟች ባለቤት፥ መንግስት አስፈላጊውን እገዛ ካደረገልን ወደ ቀያችን እንመለሳለን ብለዋል።

በሙሉጌታ ደሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.