Fana: At a Speed of Life!

በእንስሳት እርድ ወቅት ለቆዳ ጥንቃቄ እንዲደረግ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስትቲዩት ዜጎች ለበዓል በሚፈፅሟቸው የእንስሳት እርድ ወቅት ለቆዳ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጠየቀ፡፡

ድርጅቱ የቆዳ ጠቀሜታ በሕብረተሰቡ ዘንድ በስፋት እንዲታወቅ ለሕብረተሰቡ እና በዘርፉ ለተሰማሩ አካላት የተለያዩ ድጋፎችን እያደርገ መሆኑን ገልጿል፡፡

ኢንስቲትዩቱ የኮሚኒኬሽን ከፍተኛ ባለሙያ ገነት ደምሴ÷ በዘርፉ ከደረጃ አንድ ጀምሮ እስከ ማስተርስ ዲግሪ የትምህርት ስልጠናዎችን እንደሚስጥ ተናግረዋል፡፡

ሕብረተሰቡ የበሬ፣ የበግ፣ የፍየል እና የመሳሰሉት እንስሳት እርዶችን በሚፈፅምበት ጊዜ ለቆዳ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት እና በአካባቢው ለሚገኝ ተረካቢ ቆዳውን በአግባቡ ማድረስ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ለቆዳ ምርት የሚያስፈልግ እንደ ጨው ያለ የግብዓት አቅርቦት ዕጦትም ኢንስትቲዩቱ ቀርፎ በኢትዮጵያ ግብዓት ልማት ድርጅት (ኢግልድ) በኩል ለቆዳ ፋብሪካዎች እንዲቀርብ መደረጉን ተገልጿል፡፡

በሲሳይ ጌትነት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.