Fana: At a Speed of Life!

አቶ አገኘሁ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ከዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ስቴቨን ኦማም ዎሬ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ ክልል አራት ዞኖች በከፈተው ወረራ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውንና ከ4 ሚሊየን በላይ ዜጎች ደግሞ አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል፡፡

አሸባሪው ቡድን ወረራ በፈጸመባቸው ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ ሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ጎንደር እና ደቡብ ጎንደር አካባቢዎች ንጹሃንን በግፍ ገድሏል በርካቶችንም አፈናቅሏል ብለዋል ርእሰ መስተዳድሩ፡፡

መሰረተ ልማቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መውደማቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ለመልሶ ግንባታ የዓለም አቀፍ ተቋማት እና ድርጅቶች ድጋፍ አሰፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ስቴቨን ኦማም ዎሬ የጉዳቱን መጠን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ገልጸው የሰብዓዊ ድጋፍ መቅረብ ጀምሯል ብለዋል፡፡

በሰሜን ወሎ ዳውንት እና በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን 14 ከባድ ተሽከርካሪዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ይዘው ወደ አካባቢው እየደረሱ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም የችግሩን መጠን ተረድቶ ቅድሚያ ለመስጠት የተጣራ መረጃ ከክልል እና ከፌዴራል መንግሥት እንደሚፈልጉ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡

ተወካዩ ድጋፉ በሚደርስባቸው አካባቢዎች የአካባቢው የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች እና ሕብረተሰቡ ቀና ትብብር እንዲያደርጉ ስቴቨን ኦማም ዎሬ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.