Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ ከሮታሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሮታሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሼክሃር ሜሂታጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም ሼክሃር ሜሂታ ድርጅታቸው ትምህርትን ለማስፋፋት፣ ሴቶችን በማብቃት፣ ለልጃገረዶች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብ በተለያዩ ሀገራት እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
 
በተመሳሳይም በጤና በኩል በአካባቢ ጤና አጠባበቅ፣ ፖሊዬ እና ፈንጣጣ ከምድር ገጽ ለማጥፋት በተካሄዱ ዘመቻዎች እንዲሁም የተለያዩ ክትባቶችን ለማድረስ በሚደረጉ ጥረቶች ድርጅታቸው ተሳታፊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
 
በኢትዮጵያም የድርጅቱ አባላት ቁጥር እንዲጨምር እና በቀጣይ ዓመት የአፍሪካ ሀገራት የዓለም አቀፍ ሮተሪ ክለቦች በአዲስ አበባ ኮንፈረንስ እንዲያካሂዱ በመንግስት በኩል ድጋፍ እንዲሰጥ ፕሬዚዳንቱ ጠይቀዋል፡፡
 
አቶ ደመቀ በበኩላቸው የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽ እንዲሆን ድርጅቱ እያደረገ ላለው እንቅስቃሴ ምስጋና ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ድርጅቱ የኢትዮጵያ መንግስት ትኩረት በሚሰጣቸው መስኮች ላይ አተኩሮ የሚሰራ በመሆኑ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም ነው ያረጋገጡት፡፡
 
ድርጅቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሮታሪዎችንና ከ35 ሺህ በላይ ክለቦችን በማቀፍ በ200 ሀገራት የበጎ አድራጎት ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን÷ በኢትዮጵያም ለ65 ዓመታት ያህል አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.