Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን ከ1 ሺህ በላይ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን ከ1 ሺህ በላይ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የዞኑ ንግድ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የዞኑንግድ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ያህያ አባ ጨብሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷በዞኑ በ25 ሺህ 425 የንግድ ተቋማት ላይ ቁጥጥርና ክትትል ተደርጓል፡፡
በዚህም በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 1 ሺህ 427 የንግድ ተቋማት መታሸጋቸውን ነው የገለጹት፡፡
በተጨማሪም ለ221 ነጋዴዎች ማስጠንቀቂያ መሰጠቱንና 23 የሚሆኑት ደግሞ ለህግ መቅረባቸውን ጠቁመዋል፡፡
እርምጃ የተወሰደባቸው ነጋዴዎች ምክንያታዊ ያልሆነ ዋጋ የጨመሩ፣ ደረሰኝ የማይቆርጡ፣ የሸቀጦችን ዋጋ ግልፅ የሆነ ቦታ ላይ ያለጠፉና ትክክለኛ መስፈርያ የማይጠቀሙ መሆናቸውን ገለጸዋል።
በቀጣይም የኑሮ ውድነትን በመፍጠር በአቋራጭ ለመክበር በሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥርና ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሃላፊው ጠቁመዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.