Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈርያት ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ፀሐፊ ልዩ መልእክተኛ ራሚሮ ሎፔዝ ዳ ሲልቫ ጋር በሰሜኑ የኢትዮያ ክፍል በመንግስት እና የሰብዓዊ አጋሮች እየተከናወነ ባለው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እና ስርጭት ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተገለፀ፡፡
በአማራ እና አፋር ክልሎች የተጀመረውን የሰብዓዊ እርዳታ የማዳረስ ጥረት የማስፋት እና የማፋጠን አስፈላጊናትና ክንውኖች ላይ መምከራቸውን የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
በውይይታቸውም የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን እንቅስቃሴ ለማፋጠን በቅርቡ በተወሰዱ የማሻሻያ እርምጃዎች ልዩ መልዕክተኛው መደሰታቸውን እና የተሻለ አፈጻጸም መኖሩን ገልፀዋል ነው የተባለው፡፡
ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየት የመፍትሔ ሃሳብ መለዋወጣቸውንም ወይዘሮ ሙፈርያት ገልፀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.