Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስትሩ የመልካም ምኞች መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን የ2014 ዓ.ም አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለመላው አርሶና አርብቶ አደሮች የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ለመላው አርሶና አርብቶ አደሮቻችን፣ በየደረጃው ለሚትገኙ የግብርና ዘርፍ አመራሮች እና ባለሙያዎች፣ በተለይም ደግሞ ለአርሶና አርብቶ አደሮች በቅርበት ሙያዊ ድጋፍ እየሰጡ ለሚገኙ የልማት ጣቢያ ሰራተኞች፣ አጋርና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ለመላው የሀገራችን  ህዝቦች እንኳን ለ2014 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ  ብለዋል።

አዲስ ዓመት ሰላማችንን አረጋግጠን በሙሉ አቅማችን ልማታችንን የምናፋጥንበት እና በግብርናው ዘርፍ ያገኘናቸውን ውጤቶች በማስቀጠል ተጨማሪ ስኬቶች የምናስመዘግብበት ዓመት እንዲሆንልን እመኛለሁ  ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.