Fana: At a Speed of Life!

ጁንታው በወሎ ግምባር ያሰበውን ያላሳካው ጦርነቱ ህዝባዊ በመሆኑ ነው- የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ጁንታው በወሎ ግምባር ያሰበውን ያላሳካው ጦርነቱ ህዝባዊ በመሆኑ ነው ሲሉ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰይድ መሀመድ ገለጹ።

ዋና አስተዳዳሪው ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ተስፋፊና ዘራፊ ቡድኑ ከሰሜን ወሎ ተሻግሮ በደቡብ ወሎ ተሁለደሬና ወረባቦ ወረዳዎች ጥቂት ቀበሌዎች ላይ ሰርጎ ለመግባት ሙከራ ማድረጉን ገልፀዋል።

ጁንታው በገባባቸው በእነዚህ አካባቢዎች ሁሉንም አይነት ወንጀል ፈፅሟል ነው ያሉት አቶ ሰይድ መሀመድ።

በዚህም የህክምና ተቋማትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ዘርፏል፣  አውድሟል፣የተቋማት ጥበቃዎችን ደብድቧል፣  ሱቆችን ዘርፏል፣ ቤት ውስጥ ያለ የአርሶ አደር ልብስ ሳይቀር ጌጣጌጥም ጭምር አራግፎ ዘርፏል ብለዋል።

በረጅም ጊዜ ያፈራው የአርሶ አደሩ ሀብትና ንብረትን ያለርህራሄ አውደሟል ከብቶችንም ገድሏል ፣ ይህንንም በቅኝታችን አረጋግጠናል ብለዋል።

ወደ ደቡብ ወሎ ለመግባት ያደረገው ጥረት ከአንድ ወር በላይ እንደፈጀበት ያነሱት አቶ ሰይድ፥ የውጫሌን ግንባር ለመስበር ያደረገው ሙከራ የወሎ ህዝብ ባደረገው ተጋድሎና የሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ በወሰዱት የተቀናጀ እርምጃ ቡድኑ ሽንፈትንም ሞትንም ተከናንቦ እንዲመለስ ተደርጓል ነው ያሉት።

ቡድኑ ከ400 በላይ መኪኖችን አዘጋጅቶ ለመዝረፍ ተዘጋጅቶ የመጣ ቢሆንም በተከፈለው መስዋእትነት ይህ ሳይሳካ ቀርቷል ብለዋል።

ቡድኑ ፈቅዶ ሳይሆን ተዋርዶና ተቀጥቅጦ ተመልሷል ያሉት ዋና አስተዳደሪው የወረባቦና ተሁለደሬ ተራሮች ለዚህ መስክር ናቸው ሲሉም አስቀምጠዋል።

የቡድኑ የውስጥ ለውስጥ ሰርጎ ገብ  አካሄድ ያልተቋረጠ በመሆኑና በተለይም ቡድኑ እድል ከተሰጠው ዳግም የህልውና ስጋት በመሆኑ ከመዘናጋት መውጣት ይገባል ብለዋል።

በሂደቱ ቁልፍ ሚና የነበራቸውን አካላት ያመሰገኑት አቶ ሰይድ፥ በዚህ የበአል ሰሞን በቡድኑ ጉዳት የደረሰባቸውን አካላት ማሰብና መደገፍ ያስፈልጋል ብለዋል።

በጋዜጠኞች ቡድን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.