Fana: At a Speed of Life!

ዋልያዎቹ ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አባላት (ዋልያዎቹ) ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለግሰዋል፡፡

ከውዳሴ ዲያጎነስቲክ ሴንተር ጋር በመተባበር ዋሊያዎቹ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከለገሱት ደም በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት በ “መልካምነት ቀን” ህሙማን መጠየቃቸውን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአለም ዋንጫ ለማለፍ እያደረገ ባለው ጥረት በዚህ ሳምንት ከዚምባቡዌ ጋር በባህርዳር ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ 1 ለ 0 በማሸነፍ ከምድቡ ሶስት ነጥብ ይዞ ቀጣይ ግጥሚያዎችን በመጠባበቅ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.