Fana: At a Speed of Life!

የጀግንነት ቀን በአዲስ አበባ በደማቀ ዝግጅት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የጀግንነት ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ባለስልጣናትና የጦር መኮንኖች በተገኙበት በደማቀ ሁኔታ እየተከበረ ነው፡፡

የጀግንነት ቀንን ማክበር ያስፈለገው በየዘመኑ ኢትዮጵያን ከውስጥና ከውጭ ጠላት የሚታደጓትን ጀግኖች አርበኞች ልጆቿን ለማሰብ እና ለመዘከር ነው ተብሏል፡፡

በመርሐግብሩ የኢትዮጵያን ሰላምና ክብር ለማስጠበቅ የህይወት መስዕዋት የከፈሉ እና እየከፈሉ ያሉ የጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፀጥታ አካላት እንዲሁም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ብርቱ ተጋድሎ ያደረጉ የህክምና ባለሙያዎች እና ቤተሰቦቻቸው የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም ይካሄዳል።

በዝግጅቱ ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር ቀነዓ ያደታ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የመከላከያ የጦር መኮንኖች እንዲሁም ጀግኖች አርበኞች እና ሌሎች አካላት መገኘታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.