Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ ለሁለተኛ ጊዜ ለህልውና ዘመቻው ደጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁለተኛው ዙር ከህብረተሰቡ ያሰባሰበውን አንድ ቢሊየን 270 ሚሊየን የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ አስረከበ።
ድጋፉን ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ለሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ አስረክበዋል፡፡
የጀግንነት ቀን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ መርሐግብሮች እየተከበረ ነው።
የሀገሪቱን ሰላምና ክብር ለማስጠበቅ የህይወት መስዕዋት እየከፈሉ ያሉ የጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፀጥታ አካላት እንዲሁም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ብርቱ ተጋድሎ ያደረጉ የህክምና ባለሙያዎችና ቤተሰቦቻቸው የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
በመረሐግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ለሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ፣ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አባት አርበኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.