Fana: At a Speed of Life!

የአደዛዥ ዕጽ በሱዳን ድንበር እንዳይገባ እየተቆጣጠረ መሆኑን ፌዴደራል ፖሊስ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በሱዳን ድንበር   ህብረተሰቡ ጁንታው እንደ ትልቅ መሳሪያ የሚጠቀምበትን የአደንዛዥ ዕጽ እንዳይዘዋወር ድንበር ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በሱዳን ድንበር ተከዜ ማዶ የመሸገውን አሽባሪ ቡድን እቅስቃሴ በመከታተልና አጸፋዊ ምላሽ በመስጠት ተልዕኮውን እየተወጣ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ሰሜን ዳይሮክቶሬት ዲቪዥን 3 ሃላፊ ኮማንደር እንየው አለባቸው ተናግረዋል፡፡

በሁመራ ግንባር የተሰለፈው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ጁንታውና ተላላኪዎቹ በሱዳን ድንበር ወደ ሀገራችን እንዳይገቡና ወደ ሱዳንም እንዳይሻገሩ መፈናፈኛ በማሳጣት ተስፋ እያስቆረጣቸው መሆኑን ጨምረው ሃላፊው ገልጸዋል፡፡

ጁንታው በማይካድራ፣ሁመራና አካባቢው የዘር ጭፍጨፋ ፈጽሞ ወደ ሱዳን በመሻገር ሀይሉን ለማጠናከር ቢሞክርም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከአማራ ልዩ ሀይል ጋር በመሆን የወረራና የተስፋፊነት ህልሙ እንዲጨናገፍ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ጦርነቱ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቆ እንደገና ወረራ እየፈፀመ ካለ ሃይል ጋር በመሆኑ ህብረተሰቡ በንቃትና በትጋት ለሰራዊቱ መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠሉንም ጨምረው አመላክተዋል፡፡

ህብረተሰቡ ጁንታው እንደትልቅ መሳሪያ የሚጠቀምበትን የአደዛዥ ዕጽ እንዳይዘዋወር ድንበር ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል፡፡ለዚህም ለሁመራና አካባቢው ማህበረሰብ ምስጋና ይገባልም ብለዋል፡፡

ይህንን ከሃዲ ወራሪ ቡድን አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣትና እስከመጨረሻው ለማጥፋት መስዋትነትም ጭምር ለመክፈል ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ሰሜን ዳይሬክቶሬት ዲቪዥን ሶስት አመራርና አባላቱ በበኩላቸው፥ በጽፈኛው አሸባሪ ቡድን ከዚህ ቀደም ክህደት የተፈጸመባቸው በመሆኑ አሽባሪው ቡድንን መከላከል ሳይሆን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ቆርጠው መነሳታቸውን ኢ/ር ማስረሻ ሹመት ተናግረዋል፡፡

ኢ/ሩ አያይዘውም ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላትና ከሰቲት ሁመራ ህዝብ ጋር በመሆን ያሸባሪውን አከርካሪ ለመስበር ዝግጁ  ነን ማለታቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.