Fana: At a Speed of Life!

ከህልውና ዘመቻው ጎን ለጎን የመኸር ምርታችንን በእጥፍ እናሳድጋለን – የግራር ጃርሶ አርሶ አደሮች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህልውና ዘመቻውን በሚያስፈልገው ሁሉ ከመደገፍ ጎን ለጎን የመኸር እርሻ ምርታቸውን በእጥፍ ለማሳደግ እየሰሩ እንደሆነ በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ግራር ጃርሶ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች ገለፁ።

በዞኑ በሰብል ከተሸፈነው መሬት ከ10 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽህፈት ቤት ገልጿል፡፡

የወረዳው አርሶ አደሮች÷ የአካባቢያቸውን ሰላምና ፀጥታ ከማስከበር ባለፈ ለመከላከያ ሰራዊት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የህልውና ዘመቻውን እያገዙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በአንድ ሄክታር አነስተኛ ምርት እንደሚያገኙ የገለፁ አርሶ አደሮች÷ በአሁኑ ወቅት ግን ምርጥ ዘር በመጠቀምና በመስመር በመዝራታቸው ምርታቸው በእጥፍ እና ከእጥፍ በላይ እንደሚያድግ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡

የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሐብት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሂርጳሳ አዱኛ÷ ዘንድሮ ዝናቡ በመስተካከሉና የተሻለ የግብአት አጠቃቀም በመኖሩ ምርት ይጨምራል የሚል የባለሙያዎች ግምገማ እንዳለ ገልፀዋል፡፡

በምርት ዘመኑ በሰብል ከተሸፈነው መሬት ከ10 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ የተለያዩ ድጋፎች ለአርሶ አደሩ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.