Fana: At a Speed of Life!

የህልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ክልሉ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል – አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ የህልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ለሀገር መከላከያና ለሌሎች የጸጥታ ሀይሎች የሚያደረጉትን ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አስታወቁ።
ርዕሰ መስተዳድሩ አዲሱ ዓመት ለመላው የክልሉና የኢትዮጵያ ህዝብ የድልና የልማት ዘመን እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ከአሁን በፊት የክልሉ መንግስትና ህዝብ ለሀገር መከላከያና ሌሎች የጸጥታ አካላት በሰው ሃይል፣ በገንዘብ ፣ ደም በመለገሰና ሌሎች ድጋፎችን ሲያደረጉ መቆየታቸውን በዚሁ መግለጫቸው አንስተዋል።
በአዲሱ ዓመትም ህወሓት፣ ሸኔና ሌሎች የጥፋት ተላላኪዎችን እኩይ ሴራ ተቀልብሶ የህልውናው ዘመቻ በድል እስኪጠናቀቅ ህዝባዊ ደጀንነቱንና ድጋፍን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
ርዕሰ መስተዳደሩ በማያያዝ የውስጥና ውጭ ጠላቶች በሀገር ላይ የተጋረጠውን ፈተና በድል በመሻገር የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥና የብልጽግና ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ የክልሉ መንግስት ህዝቡን አስተባብሮ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቅሴዎች ተግዳሮት እየሆነ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የመከላከሉ ተግባርም ሌላው በአዲሱ በጀት ዓመት በትኩረት የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን አመላክተዋል።
ቀደም ሲል በክልሉ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅና የክልሉን ሰላም አስተማማኝ የማድረግ ተግባርም የአዲሱ ዓመት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳደሩ ገልጸዋል።
2013 ዓ.ም. እንደ ሀገር ፈተናዎች የበዙበት ዓመት ቢሆንም በርካታ የድል ስኬቶች የተመዘገቡበት እንደነበርም አውስተዋል።
አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ ጠላቶች የሚወገዱበትና የሚያፍሩበት፤ የክልሉ ብሎም ሀገሪቱ ህዝቦች ደግሞ የሚደሰቱበት ዘመን እንዲሆን ርዕሰ መስተዳደሩ መልካም ምኞታቸው መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person
0
People Reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share

0 Comments

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.