Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ አዲሱን ዓርማውን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ቀደም ሲል ይጠቀምበት የነበረውን ዓርማ መቀየሩን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው አዲሱ አርማ ከጳጉሜ 2 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ተፈፃሚ ይሆናል ነው የተባለው፡፡
በክልሉ ቀደም ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ሲጠቀምበት የነበረው አርማ የክልሉ ፖሊስ የሰነቀውን ራዕይና ተልዕኮ እንዲሁም ኮሚሽኑ ዛሬ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ የማያንጸባርቅ መሆኑ አርማውን ለመቀየር ምክንያት መሆኑንም ነው የተገለፀው፡፡
ከዚያም ባለፈ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ መልክ ያወጣቸው እሴቶች በቀድሞው አርማ ውስጥ ስለማይገኙ እና አሁን ከተደረሰበት አለም አቀፍ የፖሊስ ደረጃ ጋር የቀድሞው አርማ ያልተሳሰረና የማይገናኝ በመሆኑ አርማውን ለመቀየር መወሰኑን አስታውቋል፡፡
አዲሱን አርማ ከቀድሞ አርማ ጋር ጎን ለጎን መጠቀም የሚቻለው እስከ 6 ወር ብቻ መሆኑን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.