Fana: At a Speed of Life!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ሰራተኞች ለመከላከያ ሠራዊት ከ16ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኤጀንሲው አመራርና አባላት የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እየተፈታተነ ያለውን አሸባሪ ቡድን ለማስወገድ መስዋዕትነት እየከፈለ ላለው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ16ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው÷ መከላከያ ሠራዊቱ የሀገርን ሉዓላዊነት እንዳይደፈር ምትክ የሌለውን ህይወት እየገበረ መሆኑን ገልጸው÷ የኤጀንሲው አመራርና አባላትም ለሃገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት በፈቃደኝነት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለግሠዋል ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ኤጀንሲው በተሰጠው ሀገራዊ ተልዕኮ በህግ ማስከበር እርምጃው በተለያየ አግባብ እስከህይወት መስዋዕትነት አስተዋጽዕ እያበረከት እንደሚገኝ እና በቀጣይም የኤጀንሲው አባላት ግንባር ድረስ ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ዋና ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ በበኩላቸው በእያንዳዱ መከራ ውስጥ ቀንና ለሊት የሀገር ድንበር ሆኖ ለሚጠብቀው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኤጀንሲው አመራሮችና አባላት ስላበረከቱት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ኤጀንሲው ለሠራዊቱ ካደረገው ድጋፍ በተጨማሪ ባለቤቷ በህግ ማስከበር ሂደት መስዕዋት ለሆነ የኤጀንሲው አባል እና በህግ ማስከበሩ ሂደት ህይወቱ ለተሰዋ የቀድሞ የተቋሙ አባል ባለቤት የአዲስ አመት በዓል አስመልክቶ የገንዘብ ስጦታ መበርከቱን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.