Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ሚኒስቴር ያሳደሳቸውን የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር በክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ያሳደሳቸውን የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት አስረክቧል።
መኖሪያ ቤቶቹን የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በቦታው በመገኘት ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፥ አቅመ ደካሞችን ማገዝ ሰው የመሆንና የማህበረሰብ አካል የመሆን ጉዳይ መሆኑን ገልፀው የታደሱትን ቤቶች ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል።
አቅመ ደካሞችን ማገዝ የመንግስት ኃላፊነት ብቻ ባለመሆኑ ሁሉም ሃላፊነት እንዳለበትም ጠቁመዋል።
ከቤቱ እድሳት በተጨማሪም ለተጠቃሚዎቹ አስፈላጊ የቤት ቁሳቁሶች ተሟልቶላቸዋል።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሃና የሺንጉስ፥ የትምህርት ሚኒስቴር ላደረገው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አመስግነዋል።
በ2014 ዓ.ም የበጋ ወራትም የበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነውመረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.