Fana: At a Speed of Life!

አካባቢውን በአፍሪካ የቱሪዝም መስህብ ለማድረግ እየተሰራ ነው – ዶ/ር አብርሃም በላይ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወንጪ ደንዲ ኢኮ-ቱሪዝም ፕሮጀክት በቅድሚያ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቀሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን የፕሮጀክቱ አስተባባሪና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ።
ከ “ገበታለሀገር” ፕሮጀክት መካከል አንዱ የሆነው የወንጪ ደንዲ ፕሮጀክትን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ የወንጪ ደንዲ ፕሮጀክት አስተባባሪና የኢኖቪሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የወሊሶ ከተማ አካባቢ ሽማግሌዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
ፕሮጀክቱ የተቀረጸው የአካባቢውን ተፈጥሮ ሃብት በሚጠብቅና በሚንከባከብ መልኩ መሆኑን ዶክተር አብርሃም ተናግረዋል፡፡
በሚፈጥረው የስራ እድል የአካባቢው ማህበረሰብ ይበልጥ ተጠቃሚ በማድረግ ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ እንደሚያግዝም አብራርተዋል።
በፕሮጀክቱ አካባቢውን በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ልዩ የቱሪዝም መስህብ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የኦሮሚያ ኢንዱስትሪና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ማቲዎስ ሰቦቃ በበኩላቸው÷ ፕሮክጀቱ የአካባቢውን የተፈጥሮዊ ሃብት በመጠበቅ ረገድ የላቀ ሚና አለው ብለዋል፡፡
ዓለም ላይ ከተፈጠሩት የስራ እድሎች ውስጥ በኢኮ-ቱሪዝም 7 በመቶ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰው÷ በዚህም ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል በመፍጠር ረገድ ትልቅ እድል ይዞ መጥቷል ነው ያሉት።
የአከባቢው ማህበረሰብና አመራሮችም ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
የወንጪ ደንዲ ፕሮጀክት የአካባቢውን ተፈጥሮዊ መስህብ ይበልጥ ከማጉላት በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ትልቅ መሆኑን የፕሮጀክቱ አማካሪ ዶክተር ኢንጅነር መሰለ ሃይሌ አብራርተዋል፡፡
አሁን ላይ የመንገድ ግንባታ ስራ እየተከናውነ መሆኑንና በተያዘው በጀት ዓመትም ሌሎች የመብራትና የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
በፕሮጀክቱ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎች፣ ባህላዊ ሎጅና ሬስቶራንት፣ የአትሌቲክስ መንደር፣ የጎልፍ ክለብ ይካተቱበታል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.