Fana: At a Speed of Life!

የባህርዳር ከተማ ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የባህርዳር ከተማ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ድጋፍ አደረገ።

የባህርዳር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ባየ አለባቸው እንደተናገሩት÷ የከተማ አስተዳዳሩ 7ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ 1ሺህ 12 ኩንታል ዱቄት፣ የዕለት ምግብ ፣ሰባት ሰንጋ ፣ 40 ፍየሎች እና 59 በጎች ድጋፍ አድርጓል።

በተጨማሪም 3ሺህ የሚጠጉ አልባሳት የድጋፉ አካል ሲሆኑ÷ በማይጠምሪ ግንባር ለሚገኙ የፀጥታ አካላት እና ተፈናቃዮች ይውላል ተብሏል።

ድጋፉ ከባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች፣ ነጋዴዎች እና ከሀይማኖት ተቋማት የተሰበሰበ ነው።

ድጋፉን የተረከቡት የጎንደር ኮማንድ ፓስት አስተባባሪ አቶ ደሳለኝ አስራደ የተደረገው ድጋፉ የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው÷ አሸባሪው የህወሓት ቡድን እስኪደመሰሰ ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ጠይቀዋል።

የጎንደር ከተማ ከንቲባ ሞላ መልካሙ÷ ድጋፉ የአካባቢው ማህበረሰብ በበጎ ሲያነሳው የሚኖር ነው ብለዋል።

የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች በወሎ እና በደብረታቦር ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ተመሳሳይ ድጋፍ አድርገዋል።

በክብረወሰን ኑሩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.