Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስቴር የመስኖ ውኃ መሳቢያ ፓምፕ ጄኔሬተሮችን ለጋምቤላ ክልል አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር በ2013 በጀት ዓመት በልዩ ድጋፍ በጀት ለጋምቤላ ክልል በዕቅድ ከተያዙ 120 የመስኖ ውኃ መሳቢያ ፓምፕ ጄኔሬተሮች መካከል ወደ ሀገር ውስጥ የገቡትን 42ቱን ለክልሉ አስረክቧል።
የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና አርብቶ አደር ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን፥ ልማት የሰላም አካል በመሆኑና ጋምቤላ ክልል ሰፊ የሆነ እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በመኖሩ ሚኒስቴሩ የመስኖ ውሃ መሳቢያ ፓምፖ ጄኔሬተሮች ማበርከቱን ገልጸዋል።
እነዚህ ውሃ መሳቢያ ፓምፖ ጄኔሬተሮች ከልማት ባለፈ ለወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ትልቅ አቅም ያላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘውም በቀጣይም እነዚህን ጀኔሬተሮች ስራ ላይ ለማዋል ከሚለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ስልጠናዎች እንደሚሰጡ እና ምን ያህል በስራ ላይ ውለዋል የሚለውም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ክትትል እንደሚደረግ ገልጸዋል።
የጋምቤላ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኋላፊ አቶ ኡጁሉ ሉዋል በበኩላቸው፥ በክልሉ ዓመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞች የሚገኙበት አካባቢ እንደመሆኑ የተበረከቱልን የእርሻ መሳሪያዎች የክልሉን ልማት ለማፋጠን ትልቅ አስተዋኦ አለው ብለዋል።
ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ለክልሉ ላበረከተው ድጋፍም ማመስገናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
165
Engagements
Boost Post
160
1 Comment
4 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.