Fana: At a Speed of Life!

ከ8 ሚሊየን ሊትር በላይ ዘይት ለህብረተሰቡ ሊቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘመን መለዋጫ በዓልን አስመልክቶ ሸማቾች በተረጋጋ መልኩ እንዲውሉ ቅንጅታዊ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን በፌደራል ደረጃ የተቋቋመው የገበያ ማረጋጋት ግብረ ሃይል አስታወቀ፡፡
ግብረ ኃይሉ ባለፉት ሳምንታት ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ ለንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ባቀረበው ሪፖርት እንዳመላከተው÷ የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይፈጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በዚሁ መሰረት የኢትዮጵያ ቄራዎች ድርጅት 1ኪሎ የበግ ስጋ በ210 ብር እንዲሁም 1ኪሎ የበሬ ስጋ በ280 ለመሸጥ ስምምነት ላይ መደረሱንም ግብረ ኃይሉ ጠቁሟል፡፡
በህብረት ስራ ማህበራት በኩል ቀይ ሽንኩርት ከ27-28 ብር፣ ነጭ ሽንኩርት ከ80-85 ብር፣ ነጭ ጤፍ በኩንታል ከ4200-4400 ብር፣ ሰርገኛ ጤፍ በኩንታል ከ4050-4200 ብር ቀይ ጤፍ ከ3700-3900 ብር ለመሸጥ ከስምምነት ተደርሷል ነው ተባለው፡፡
በተጨማሪም የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ የዘይት አቅርቦት ችግር እንዳይከሰት ከውጪ ከሚገባው ዘይት በተጨማሪ በሀገር ውስጥ የተመረተ 8 ነጥብ 7 ሚሊየን ሊትር በመንግስት ዋጋ ለህብረተሰቡ ለማከፋፈል ዝግጅት ተጠናቋል መባሉን ከንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.